በኢትዮጵያ ያሉ
የአካል ጉዳተኞች

ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ደሀ ሀገሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡

ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች የኑሮ ሁኔታው በተለየ መንገድ ከባድ ነው፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ኑሮ ነው የሚኖሩት፤ ያለመንግስት ድጋፍ በራሳቸው እንዲፍጨረጨሩ ወይም በቤተሰብ ድጋፍ ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ነው የሚተዉት፡፡ የእርዳታ በተለይም የዊልቸር እርዳታዎች ክፍተት ከፍተኛ ነው፡፡ የጤና እና የህክምና እንክብካቤዎች በጥቂቱ ነው የሚገኙት ወይም በጣም ውድ ናቸው፡፡ ይህም በጤና ብሎም በማህበራዊ ትስስር ቅቡልነት እና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ አሉታዊ የሆነ ተጽእኖ አለው በተጨማሪም የትምህርት፣ የመማር ወይም የመቀጠር እድሎች በጣም የተገደቡ ናቸው፡፡ ይህም ራስን የማስተዳደር እና የተከበረ ህይወት የመምራት እድልን ጉልህ በሆነ ሁኔታ ይቀንሰዋል፡፡ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ልጆች በተለይም ተጋላጭ ናቸው፡፡ ለእነሱም ሆነ ለቤተሰባቸው የሚደረግ ድጋፍ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ እርዳታዎች ውስን ናቸው፣ በልጆች እና በታዳጊዎች ዘርፍ ያለ የህክምና እንዴት መሆን እንዳለበት መረዳት (ቴራፒዩቲክ ኖው ሃው) አናሳ ነው እና አስፈላጊ ለሆነው ቀዶ ህክምና የሚደረገው የመጠበቂያ ጊዜም ረጅም ነው፣ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ልጆች የሚሆኑ የመዋእለ ህጻናት፣ የቀን መዋያ ማእከላት እና ትምህርት ቤቶች አናሳ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ካሎሪ ያለው የህጻናት ምግብ እና የእንክብካቤ ምርቶች በድህነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መግዛት አይችሉም፡፡ ወላጆች ብቻ አይደለም ከጥያቄያቸው እና ከስጋታቸው ጋር የሚተዉት፣ ነገር ግን ይገለላሉ፣ የጸጸት እና የሀፍረት ስሜት ይሸከማሉ፣ ስለሆነም ብዙዎቹ ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ ይደብቃሉ፡፡