አካታች የሆነ
የመጫወቻ ሜዳ

አካታች የሆነ የመጫወቻ ሜዳ/የአካል ጉዳት ላለባቸው እና ለሌለባቸው ልጆች የሴንሰሪ እና የመጫወቻ መናፈሻ በህዳር 2012 ከኩኩክ የባህል ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ከተግዳሮት ነጻ የሆነ የመጫወቻ ሜዳን ገንብተናል፡፡ በአካባቢው ከሚገኙ የተፈጥሮ እቃዎች በመጠቀም ብቻ በህክምና፣ትምህርት እና የስነ-ምህዳር ዘርፎችን ባማከለ ሁኔታ ነበር የተገነባው፡፡ ከቤት ውጪ የሆነው የመጫወቻ ስፍራ በተሃድሶ ፕሮግራም ውስጥ ላሉት ልጆች አዲስ የስሜት ህዋሳት የማነቃቃት እና የእንቅስቃሴ ልምምድ ብቃትን እንዲለማመዱ ያደርጋል፡፡ ለወደፊቱ በአካባቢው ያሉ ልጆች መጫወቻ ሜዳችን መተው እንዲጫወቱ እንጋብዛለን፡፡ ይህም የአካል ጉዳት ያለባቸው እና የሌለበናቸው ልጆች የሚኖራቸውን ቅርርብ ያጎለብታል፡፡