ኢትዮጵያ
የብዙ ሀገር መነሻ

ኢትዮጵያ በአለም ላይ ቀደምት፣ በጣም የተለያየ ባህል ካላቸው እና ሳቢ ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ በታሪክ ወደኋላ ስንሄድ ከ3000 አመት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ አላት፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በቀኝ ግዛት ካልተገዙ ሁለት ሀገሮች ኢትዮጵያ አንዷ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች በራስ የመተማመን፣ የጽናት እና የነጻነት ምልክት አድርገው ይወስዷታል፡፡ባህሏ እና ልማዶቿ በሀይል አልተቀየሩም ወይም አልጠፉም፡፡ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ካሉ ቀደምት የክርስትና ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ ክርስትና አክሱም የሚኘው የአቢሲኒያ ስርወ መንግስት ይፋዊ የመንግስት ሀይማኖት የሆነው በ4ኛው አመተ ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ብዙ መቶ አመታትን ያስቆጥሩ ብዙ የክርስትና ወጎች እና ልማዶች አሁንም በሰፊው ይተገበራሉ፡፡

ብሎም በአለም ላይ የታወቀችው የሉሲ ቅሪት አካል (የአስትራሎፒቲከስ አፋራንሲስ ቅሪት) ሌሎች የቅሪት አካል ግኝቶች ኢትዮጵያ  ቀደምት የጥንት እና “የሰው ዘር መገኛ” ለመባል ብቁ መሆንዋን ያሳያል፡፡ ምክንያቱም ትንሽ፣ አጭሯ ሴት የሰው ልጅ ታሪክ ከ3.2 ሚሊየን አመት በፊት እንደጀመረ እና አለም ላይ ያሉ ህዝቦች እንዳለ አንድ አይነት መገኛ እንዳላቸው ስለምታረጋግጥ ነው፡፡ “ሉሲ” የሚለው ቅጽል ስም የተሰጠው የቅሪት አካል ቁፋሮን የሚያደርጉት ሳይንቲስቶች በጊዜው “ሉሲ ኢን ዘ ስካይ ዊዝ ዳይመንድስ” የሚለውን የቢትልስ ዘፈን በማዳመጥ ላይ እያሉ የሉሲን ቅሪት አካል በማግኘታቸው ነው፡፡ ሉሲ በእያንዳንዱ ህጻናት ሊባል በሚችል ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ ናት፡፡ ትከበራለች እና በዚህም የሴቶች የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን “የሉሲ ቡድን” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

ኢትዮጵያ በሱማሊያ፣ በኬንያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በኤርትራ እና በጅቡቲ የምትዋሰን በአህጉሩ ሰሜናዊ ምስራቅ ላይ ያለች ወደብ አልባ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ናት፡፡ በመጠን የጀርመንን ሶስት እጥፍ ታክላለች፡፡ ከሀገሪቱ ጠቅላላ ስፋት 5 በመቶ የሚሆነው ከባህር ጠለል በላይ 3500 ሜትር ከፍታ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ የሀገሪቱ ከፍተኛው ቦታ የሆነው ራስ ዳሽን 4500 ከፍታ አለው፡፡ ብሎም ከባህር ጠለል በታች 125 ሜትር የሆነው በአለም ላይ ረባዳ እና ሞቃት የሆነው ዳናኪ ሸለቆ የሚገኘው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ የተለያዩ ከፍታዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት አይነት የአየር ንብረት ክልል እንዲኖር አድርገዋል፡፡ በዋነኛነት በሰሜን እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኘው 1500 ሜትር ላይ የሚገኘው ከፍታ የትሮፒካል ሞቃታማ የአየር ክልል ሲሆን ይህም በአካባቢው አጠራር ቆላ በመባል ይታወቃል፡፡

አማካኝ አመታዊ ሙቀቱ 27 ዲግሪ ሴልሺየስ ወይም ከዚያ በላይ ነው፡፡ ከ1500 እስከ 2500 ሜትር ከባህር ጠለል ወለል በላይ ያለው ከፍታ የሞቃት ቴምፕሬት የአየር ክልል (ወይናደጋ) ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ማእከላዊ ስፍራ ይገኛል፡፡ አማካኝ ሙቀቱም ከ20 እስከ 25 ዲግሪ ሴሊሺየስ ነው፡፡ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ አየር ንብረቱ ቀዝቃዛ ነው፡፡ አማካኝ ሙቀቱ 16 ዲግሪ ሴንቲግሬድ (ደጋ) ነው፡፡ ከ3900 ሜትር በላይ የሆኑ ከፍታዎች ላይ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች እና በረዶ ይጥላል፡፡ ሁለት ወቅቶች አሉ፡፡ ከህንድ ውቅያኖስ እርጥበት አዘል አየል ይዞ የሚነፍሰው እና ከፍተኛ ዝናብ የሚሰጠው የደቡባዊ ምስራቅ ንፋስ ከግንቦት እስከ መስከረም ያለውን የክረምት ወቅት ይሰጣል እና ከጥቅምት እስከ ግንቦት ያለው ደግሞ ደረቅ የሆነ ወቅት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ ከ2200 እስከ 3000 ሜትር ከፍታ ላይ በመገኘት በአፍሪካ ከፍታ ላይ ያለች ዋና ከተማ ነች፡፡

ህዝብ ብዛት ኢትዮጵያ በጂኦሎጂ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ባህሎቿ፣ ብሄረሰቦች እና ቋንቋዎች ልዩ የሆነች ሀገር ናት፡፡ በገለጻው መሰረት ሀገሪቱ ከ80 በላይ የሚጠጉ ብሄርብሄረሰቦች አሏት፡፡

ከጠቅላላው ህዝብ ብዛት ከ80 ፐርሰነት በላይ የሆነው በገጠራማ አካባቢ ነው የሚኖረው እና በዋነኛነት በግብርና ላይ ጥገኛ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ነው የሚቆጥረው፡፡ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከኮፕቲክ ዘመን አቆጣጠር ይለያል እና በ12 ወራት ፈንታ 13 ወራት አሉት፡፡ የመጀመሪያዎቹ 12 ወራት እያንዳንዳቸው 30 ቀናት አሏቸው እና 13ኛው ወር 5 ቀናት ሲኖራት (በየአራት አመቱ 6 ቀን ይኖራታል)፡፡ሌላኛው ልዩ የሚያደርጋት የዘመን አቆጣጠሯ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከጎርጎሮሳዊያን የዘመን አቆጣጠር የ7 አመት ልዩነት አለው ፡፡

በመሆኑም ሀገሪቷን ሲጎበኙ ቢያንስ 7 አመታትን ከእድሜዎት ላይ ወጣት ይሆናሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የሰአት አቆጣጠሩ ለየት ይላል፡፡ ሀገሪቱ የምድር ወገብ ላይ ስለምትገኝ አመቱን ሙሉ የቀን እና የሌሊት ርዝማኔ እኩል ነው፡፡ ቀኖቹ በ12 ሰአት እና ሌሊቶቹ በ12 ሰአታት ይከፋፈላሉ፡፡ ቀኑ ልክ ጸሃይ ስትወጣ 12 ሰአት ላይ ይጀምራል፡፡ በሀገሪቱ በሙሉ ዘመን አቆጣጠር እና የጊዜያት “አንድ ላይ ነው የተቀናጁት” ስለሆነም ጊዜው እና ቀኑ ምን ማለት እንደሆነ ሁሉም መረዳቱን ያረጋግጡ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በዩኔስኮ እውቅና ያገኙ 9 የሚዳሰሱ እና አራት የማይዳሰሱ የአለም አቀፍ ቅርሶች አሉ፡- አክሱም፣ በጎንደር አካባቢ የሚገኘው የፋሲል ግንብ፣ የሀረር ታሪካዊ ከተማ፣ የኮንሶ ባህላዊ መልከአምድር፣ የታችኛው አዋሽ ፣የኦሞ ሸለቆ፣ በላሊበላ የሚገኝ ውብ አብያተ ክርስትያናት፣ የጥያ፣ የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ መስቀል፣ ኢሬቻ፣ ፊቼ-ጨምባላላ እና ጥምቀት ናቸው፡፡

ተጠቃሽ ከሆኑት ዝርዝሮች ውስጥ የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርከ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ቦታዎች፣ ልዩ የሆነው የትግራይ የመሬት መልክአምድር፣ መልከአቆንጥር እና ባልጭት፣ የጌዲኦ ባህላዊ መልክአምድር፣ የይሃ ታሪካዊ ቅርስ እና በጣና ሀይቅ ውስጥ ደሴት ውስጥ የሚገኙ ገዳማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በጣም የሚጎበኙ እና የሚያስደንቁ ነገሮች አሉ፡፡

ከሁለት አመት በፊት በ2012 ኢትዮጵያ በአለም ላይ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ከነበሩ ሀገሮች አንዷ ነበረች፡፡ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ያልበለጸገች አገር ብትሆንም ነገር ግን መጠናቸው በጣም የሚለያይ እንደ ወርቅ፣ ማንጋኒዝ፣ ፕላቲንየም፣ ኮፐር፣ ፖታሽ፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን ታወጣለች፡፡

የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ አበባ፣ አነቃቂ የሆነው ጫት ፣ ሌዘር እና የሌዘር ምርቶች፣ ወርቅ እና ብሎም ቡና ወደ ውጪ ትልካለች፡፡ ይህም ያለጥርጥር የሀገሪቱ ጠቃሚ የሆነ የኤክስፖርት ዘርፍ ነው፡፡  በኢትዮጵያ ግብርና የኢኮኖሚው በጣም ወሳኝ የሆነ ዘርፍ ነው፡፡ የግብርና ምርት በኢትዮጵያ ለምግብ ዋስትና ሚና ይጫወታል፡፡ 80% የሚጋው የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ናት እና በተለያዩ የቡና አይነቶች በአለም ላይ ታዋቂ ናት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ቡና ብዙውን ጊዜ ከተፈጥሮ ጫካ ነው የሚለቀመው እና በጸሃይ ነው የሚደርቀው፡፡ ብዙዎቹ የቡና አይነቶች ከተገኙባቸው አካባቢዎች ለምሳሌ ይርጋጨፌ፣ ሲዳሞ እና ሊሙ በመባል ስያሜን ያገኛሉ፡፡ ብዙ ቡና ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ ከሚገኘው ተራራማ አካባቢ እና በዚያ ከሚገኘው ሀረር ከሚባለው ከተማ ይመጣል፡፡ የታጠበው እና የጫካ ቡና በደቡባዊ ምእራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙት ተራራማ ብዙ ዝናብ ከሚያገኙ ጫካዎች ይለቀማል፡፡ የጫካ ቡናዎች ከተተከሉ ከ9 ወራት በኋላ ቀይ ፍሬ ያፈራሉ፡፡ ከቡና ፍሬው ውስጥ ሁለት ዘሮች አሉ፤ እነዚህም የታወቀውን ትኩስ መጠጥ የሚሰጠው የአረንጓዴ ቡና ፍሬ ነው፡፡ ከሀረር አካባቢ የሚገኘው ደረቀው በሂደት ያለፈው ቡና ደግሞ ልዩ የሆነ እና ሚስጥራዊ የሆነ ጣእም አለው፡፡ ሀገሪቱ የታጠበ ቡና ልዩ ናቸው፡- ቃናቸው ጎላ ያለ ነው፣ በጣም ይጣፍጣሉ፣ የሎሚ እና የአበባ ቃናም አላቸው፡፡ ቡናን በጋራ መጠጣት የኢትዮጵያ ባህል ወሳኝ አካል ነው እና በመደበኛነት ለወዳጅነት፣ አብሮ ለመሆን እና ለመጋራት በቀን ሶስቴ ይከወናል፡፡ ጥብቅ የሆነ ስርአቶች ይተገበራሉ፣ ይህም ቡናውን በሚገባ በማጠብ እና አረንጓዴውን፣ ጥሬ ፍሬውን በማድረቅ ይጀመራል ከዚያም ማንደጃ ላይ በማድረግ በእሳት በብረት ምጣድ ላይ በብረት ቡና መቁያ ይቆላል፡፡

ጣፋጭ የሆነ ቃና ያለው ሽታ እስኪሰጡ ድረስ ቡናዎቹ ብረት ምጣዱ ላይ በቡና መቁያው ወደ ፊት እና ወደ ኋላ እየተደረጉ ቡናው እየተገላበጠ ይቆላል፡፡ የተቆላ እና እየጨሰ ያለ ቡናን የያዘው የቡና ማንከሽከሻ ክብ ሰርተው በተቀመጡ ሰዎች ፊት ይዞራል እና በዚህ ስርአት ላይ የተገኙት ሁሉም ይህን አስገራሚ ሽታ እንዲያሸቱ እና ደስ እንዲሰኙ ይደረጋል እና ከዚያም “ጀበና” ተብሎ በሚጠራው ክብ አንገት ያለው የሸክላ እቃ ውስጥ ውሃው እየፈላ እያለ የተቆላው ቡናው በሙቀጫ ይወቀጣል (ነገር ግን አይደቅም!)፡፡ የተወቀጠው ቡና እሳት ላይ በተቀመጠው እና ውሃ በማሞቅ ላይ ባለው ጀበና ውስጥ ይጨመራል እና የተወቀጠው ቡና ከተጨመረ በኋላ እንዲጠል ይደረጋል ከዚያም በ30 ሴንቲሜትር እርቀት ላይ በስኒ እንዲቀዳ ይደረጋል፡፡ የጓሮ ተክሎች ቡና ውስጥ ይጨመራሉ ወይም በቅቤ እና በጨው እንዲጣፍጥ ይደረጋል፡፡ በቡና ስነ ስርአት ወቅት ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት አለበት፡፡ እያንዳንዱ ስኒ ቡና የራሱ የሆነ ትርጓሜ አለው፣ የመጀመሪያው አቦል በመባል ይታወቃል እና ጠንካራ የሆነ ቡና ነው ይህ ለደስታ ብቻ ነው የሚጠጣው ሁለተኛው መለስ ያለ ቡና ደግሞ ቶና ይባላል እና ስለችግሮች እና ስጋቶች ለማውራት ጊዜ ይሰጣል፡፡ በረካ፣ ሶስተኛው ዙር ቡና ነው፡፡ እና የተገኙትን ሰዎች ሁሉ ለማመስገን እና ለመባረክ ያገለግላል፡፡ ቢያንስ ሶስት ስኒ ቡና ሳይጠጡ ከቡና ስነ-ስርአቱ መነሳት ተገቢ አይደለም ተብሎ ይታሰባል፡፡ ኢትዮጵያኖች ሶስቱንም ዙር ቡና ሲጠጡ መንፈሳቸው እንደሚታደስ ያምናሉ፡፡

እንጀራ ብዙውን ጊዜ ቀዝቃዛ ሆኖ የሚበላ መረር የሚል፣ የተብላላ ፓንኬክ መሳይ ጠፍጣፋ ዳቦ እና በከፊል ስስ የሆነ ገጽታ ያለው በልዩ መጋገሪያ የሚጋገር ምግብ ነው፡፡ በሌሎች ስፍራዎች ሩዝ፣ ዳቦ ወይም ድንች ቋሚ ምግብ እንደሆነ እንጀራም እንዲሁ በኢትዮጵያ ቋሚ ምግብ ነው፡፡ ለኢትዮጵያኖች ያለእንጀራ ቀኑ ደስ የሚል ቀን አይሆንም፡፡ እንጀራ የሚሰራው በኢትዮጵያ ብቻ በሚበቅለው ትንሽዬ የማሽላ ቅንጣት በሆነው ጤፍ ነው፡፡ እንጀራ የመመገቢያ ሳህን የሚያክል መጠን አለው፡፡ እና ብዙውን ጊዜ ቅመም በበዛበት የስጋ ወጥ ወይም የአትክልት ወጥ እና ቅመም በበዛበት የበርበሬ ድልህ ይበላል፡፡ በጋራ መብላት ማለት ከሳህን ላይ በእጅ መብላት ወይም ሌላ ሰው ሲያጎርስ መጉረስ ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ ልማድም ጉርሻ ማለትም “አፍን በምግብ መሙላት” ማለት ነው፡፡ እና ለሆነ ሰው ያለንን ክብር የምንገልጽበት መንገድ ነው፡፡ የጤፍ ሰብል በኢትዮጵያ ውስጥ ለብዙ ሺህ አመታት ሲበቅል ነበር ጤፍ “ጠፋ” ከሚል የአማርኛ ቃል ነው የተገኘው፡፡ በሚታጨድበት እና በሚወቃበት ጊዜ የአሸዋ ቅንጣት የሚያክል መጠን ያለው የጤፍ ዘር መጥፋቱ ስለማያስገርም ነው፡፡ ጤፍ ከግሉቲን ነጻ የሆነ፣ በፕሮቲን፣ በፋይበር እና በማእድናት የበለጸገ ነው፡፡ በደም ውስጥ ያለ የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር እና ምግብ የመብላት ፍላጎትን ለመመለስ ይረዳል ስለሆነም ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል፡፡ የስርአተ ልመት  ሂደትን ያፋጥናል፡፡ ከብዙዎቹ ሰብሎች በበበለጠ የተሻለ ካልሲየም ይሰጣል፣ ጡንቻን፣ ህብረ ህዋስን እና መገጣጠሚያዎችን ያድሳል እና ቁስለትን የመከላከል ብቃትም አለው፡፡ አሁን ላይ ጤፍ በአውሮፓ ውስጥ ምርጥ የሆነ መብል ሆኗል፡፡