የተልእኮዋችን መግለጫ

ተልእኮ - ግብ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሰዎችን ለመርዳት እንተጋለን፡፡ በተግባሮቻችን የደንበኞቻችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል እና በተባበሩት መንግስታት ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሰዎች መብቶች ማእቀፍ መሰረት ንቁ እና በራስ ተነሳሽነት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ በማህበራዊ ህይወት ላይ እንዲያሳድጉ እንፈልጋለን፡፡ የሰዎችን ክብር እንጠብቃልን እና ራሳቸውን ብሎም ሌሎችን የሚረዱበትን ብቃት እንደግፋለን፡፡

መርሆች - እሴቶች

በሰብአዊነት ከመድሎ ነጻ በሆነ እና ገለልተኛ እና እራሱን በመቻል መርሆች እንመራለን፡፡ በዘራቸው፣ በሀይማኖት ወይም በፖለቲካዊ እሳቤያቸው ሰዎችን ሳንፈርጅ እና መደሎ ሳንፈጽም በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ለመርዳት እንተጋለን፣አመለካከታችን እና ተግባሮቻችን በአክብሮት፣ በትብብር፣ በነጻነት፣ በእኩልነት፣ በመቻቻል እና በፍትህ እሴቶች የተቃኙ ናቸው፡፡

ተደራሽ የሚሆኑ ቡድኖች - የስራ ቦታዎች

የተግባሮቻችን ተደራሽ የሆኑ ቡድኖች አካል ጉዳተኞች ብቻ ሳይሆኑ ቤተሰቦቻቸው እና በአካባቢያቸው የሚኖሩ ሌሎች ሰዎችን ያጠቃልላል፡፡ አንኳር የሆኑ ተግባሮቻችን፡- ለመራመድ የሚያስችሉ ድጋፎችን፣ በፊዚዮቴራፒ እና በማህበራዊ ስነ-ልቦና ዘርፎች በራሳቸው እንዲቀጠሩ የሚያስችሉ የተቋማዊ የስልጠና መርሃ ግብሮችን እና ድጋፎችን፣ የእለት ተእለት ህይወትን እና የስፖርት እንቅስቃሴዎችን የሚያጎለብቱ ድጋፎችን ለደንበኞቻችን መስጠትን ያካትታል፡፡

ሰራተኞች - ቡድን

ሰራተኞቻችን በሙያቸው አስፈላጊ የሆነ ክህሎት አላቸው እና የራሳቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ፡፡ ቀጣይነት ባላቸው ስልጠናዎች ብሎም ልምድ ባካበተ የመማማር ስርአት ለመሳተፍ ሙያዊ እና የግል እድገትን እናበረታታለን፡፡ እውቀትን መለዋወጥ ቀጣይነት ያለው እድገት እና ብቃትን ማጎልበት ብሎም የቡድን መንፈስን ለማጠናከር ይረዳል፡፡ እያንዳንዱ ሰራተኛ ከራሱ ተግባር ባሻገር የእሱን ወይም የእሷን የስራ አጋር ተግባራት ያውቃል፡፡

ተቋም - ትብብር

ተግባቦት፣ ትብብር እና ግልጽነት ለእኛ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡ ራሳችንን እንደ ተማሪ ተቋም ነው የምናየው፡፡ በአንድ በኩል የተረጋገጠ ተቋምን በመያዝ ከእኛ ጋር በሚሳተፉት ሰዎች ጥራት ያለውን ህይወት እና በሌላ ጎኑ በለውጥ፣ በተሃድሶ እና ነገሮችን ለማቅናት ፈቃደኛ በመሆን ጉልህ የሆነ ስኬትን አስመዝግበናል፡፡ ሰብአዊ ተግባራትን በማሟላት ረገድ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ ባለስልጣን መ/ቤቶች ንቁ እና ገለልተኛ አጋር ነን፡፡ ሰበአዊ ድጋፍ ከሚያደርጉ ከሌሎች ተቋማት ጋር ግልጽ እና ተአማኒነት ያለው ትብብር አለን፡፡

ማህበረሰብ

በስራችን ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተሳትፎ አድርገናል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ አካል ጉዳተኛ በሆኑ እና ባልሆኑ ሰዎች መሃከል በጋራ መኖር እና መከባበር እንዲኖር ሰርተናል፡፡ በከፍተኛ ጥንቃቄ ይህንን ለማድረግ ተግተናል፡፡