የድጋፎቹ
አቅርቦት

የአዲስ ጉዞ ማእከል በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት በጣም ድሆች ከሚኖሩነት ሰፈሮች ውስጥ በአንዱ ይገኛል በከተማዋ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ይገኙባታል፡፡ አጋዥ የሆኑ መሳሪያዎቻችንን ዋንኛ ግብ ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሰዎችን እንቅስቃሴ ለማሻሻል እና ለማረጋገጥ ነው፡፡ መንቀሳቀስ መቻል ለሚከተሉት ቅድመ ሁኔታ መሆኑ አሳምኖናል፡-

° ራስን ለመቻል፤

° ትምህርት ለማግኘት፤

° በማህበረሰቡ ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን፤

° ለማህበራዊ እና ሙያዊ ትብብሮች፡፡

ልዩ ልዩ ምርቶች እና የጥገና አገልግሎት የሚሰጠው አዲስ ጉዞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች አንዱ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ በየአመቱ በቀላሉ ሊለመዱ ሚችሉ ወደ 700 የሚጠጉ ዊልቸሮችን እናቀርባለን፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ከምናደርገው ስራ በተጨማሪ ኦሮሚያ ውስጥ ለሚገኙ አምስት ሌሎች ከተሞች እናቀርባለን እነዚህም አዳማ፣ ፊቼ ፣ ቢሾፍቱ፣ አምቦ እና ሰበታ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የዊልቸር ወርክሾፕ ውስጥ 7 የዊልቸር መካኒኮች ይሰራሉ፡፡ በአዲስ ጉዞ ስራቸውን በጀመሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በማይታወቀው ሙያ “በዊልቸር መካኒክስ” መሰረታዊ ስልጠና አጠናቀዋል፡፡ ከውጪ በመጡ አሰልጣኞች ተጨማሪ ስልጠናዎች ልምዳቸውን እያሰፉ እና እያጎለበቱ ነው እና አሁን ላይ እውቀታቸውን ወደ ሌሎች የማስተላለፍ እና ሌሎች ባልደረቦችን የማሰልጠን ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡

ሙያዊ ምዘና
እና ብቁነት

በዊልቸር ሙያዊ ብቃትን መያዝ ተያይዞ የሚርሰውን ተጓዳኝ አካላዊ ጉዳት ለመከላከል፣ በቤተሰቦች እና በተንከባካቢዎች ላይ ያለውን ሸክም ለማቃለል የሚመለከታቸውን ሁሉ የህይወት ጥረት ለማሻሻል ይጠቅማል፡፡ ምቹ የሆኑ ድጋፎች ውስን በሆኑበት እና የተሃድሶ ቴክኒሺያንነት ሙያ በስፋት በማይታወቅበት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት በዊልቸር ሙያ ብቁ መሆን ክብር ነው፡፡ በጥንቃቄ ግምገማ ከተደረገ በኋላ የዊልቸር መካኒኮቻችን ከተለያዩ ሞዴሎች ውስጥ ምቹ  የሆነውን ዊልቸር ይመርጣሉ፣ ይህም በተጠቃሚዎቹ የግል ፍላጎት መሰረት ይሻሻል ወይም በተጨማሪ አንዳንድ ነገሮች እንዲገጠሙበት ይደረጋል፡፡

የጥገና
አገልግሎት

የወርክሾፓችን የጥገና አገልግሎት ለሁሉም የዊልቸር አይነቶች በሚባል ደረጃ ነጻ የሆነ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ አጋራችን የሆነው የሆሌድ ድርጅት አስፈላጊ የሆኑ መለዋወጫዎችን ያቀረብልናል፡፡ በየአመቱ ወደ 2000 የሚጠጉ ጥገናዎችን እናከናውናለን፡፡ ለዚህ አገልግሎት ምስጋና ይግባው እና የሚቀርቡት ድጋፎች ለብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

የድጋፊ መሳሪያዎቹ
ግዢ

አጋራችን የሆነው የሮሌድ ድርጅት (ኢንተርላክኢን/ስውዘርላንድ) ዊልቸሮችን እና ሮሌተር፣ መራመጃ፣ ምርኩዝ፣ የሽንት ቤት ወንበር ወዘተ የመሳሰሉትን ተጨማሪ ደጋፊ መሳሪያዎችን ይሰበስባል፡፡ እነዚህ ለወጣት ሰዎች እና ጎልማሶች ማህበራዊ እና ሙያዊ የትብብር ፕሮግራም እንደቅድመ ሁኔታ አካል የሚታዩ ናቸው፡፡ ከዚያም በኮንቴነር ተጭነው ወደ ኢትዮጵያ ይላካሉ፡፡ መጠገን የማይችሉት ድጋፍ ሰጪ መሳሪያዎች አካላቸው ይፈታታል እና በአዲስ አበባ የሚገኘው የመለዋዋጫ መጋዘን እንዲከማቹ ይደረጋል፡፡ በጣም ውስን በሆኑ አጋጣሚዎች አዲስ መለዋወጫዎችን እንገዛለን (ለምሳሌ ደረቅ እና በአየር የሚሞላ ጎማ)፡፡ ለመራመድ የሚያግዘው ከፍተኛው እርዳታ የሚመጣው ለአካል ጉዳተኞች እና እድሜያቸው ለገፉ ድጋፍ በስዊዝ ሰራተኞች ቡድን በሚተዳደረው ከስዊዝ የአካል ጉዳተኞች መድህን (አይቪ) እርዳታ ማከማቻ ነው፡፡  ሌሎች ድጋፎች በተሃድሶ ቴክኖሎጂ፣ እድሜያቸው የገፋ እና አካል ጉዳተኛ ሰዎች ተቋም ልዩ ከሆኑ መጋዘኖች ብሎም ከግለሰቦች ነው የሚገኘው፡፡ እቃዎቹ ከቀረጥ ነጻ ሆነው በሮሌድ ለአዲስ ጉዞ ነው የሚቀርቡት፡፡