የድጋፎቹ
አቅርቦት

የአዲስ ጉዞ ማእከል በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት በጣም ድሆች ከሚኖሩነት ሰፈሮች ውስጥ በአንዱ ይገኛል በከተማዋ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ይገኙባታል፡፡

አጋዥ የሆኑ መሳሪያዎቻችንን ዋንኛ ግብ ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሰዎችን እንቅስቃሴ ለማሻሻል እና ለማረጋገጥ ነው፡፡ መንቀሳቀስ መቻል ለሚከተሉት ቅድመ ሁኔታ መሆኑ አሳምኖናል፡-

° ራስን ለመቻል፤

° ትምህርት ለማግኘት፤

° በማህበረሰቡ ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን፤

° ለማህበራዊ እና ሙያዊ ትብብሮች፡፡

ልዩ ልዩ ምርቶች እና የጥገና አገልግሎት የሚሰጠው አዲስ ጉዞ በአዲስ አበባ ውስጥ ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች አንዱ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ቦታዎች አንዱ ነው፡፡ በየአመቱ በቀላሉ ሊለመዱ ሚችሉ ወደ 700 የሚጠጉ ዊልቸሮችን እናቀርባለን፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከምናደርገው ስራ በተጨማሪ ኦሮሚያ ውስጥ ለሚገኙ አምስት ሌሎች ከተሞች እናቀርባለን እነዚህም አዳማ፣ ፊቼ ፣ ቢሾፍቱ፣ አምቦ እና ሰበታ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዊልቸር ወርክሾፕ ውስጥ 7 የዊልቸር መካኒኮች ይሰራሉ፡፡ በአዲስ ጉዞ ስራቸውን በጀመሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በማይታወቀው ሙያ “በዊልቸር መካኒክስ” መሰረታዊ ስልጠና አጠናቀዋል፡፡ ከውጪ በመጡ አሰልጣኞች ተጨማሪ ስልጠናዎች ልምዳቸውን እያሰፉ እና እያጎለበቱ ነው እና አሁን ላይ እውቀታቸውን ወደ ሌሎች የማስተላለፍ እና ሌሎች ባልደረቦችን የማሰልጠን ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡