የአዲስ ጉዞ ቦርድ ከኢትዮጵያ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን ያቀፈ ነው። ሁሉም አባላት ራሳቸው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ፣ እዚያ የኖሩና የሰሩ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ሁኔታ አስቀድመው ያውቃሉ። የእነርሱ ተሳትፎ በፈቃደኝነት ነው እናም ነገሮች በዝግመተ ለውጥ እና መሻሻል እንደሚችሉ፣ እናም እያንዳንዱ ትንሽ የለውጥ እርምጃ ትልቅ ግምት የሚሰጠው እና በአንድ ግለሰብ ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ከጥልቅ ጽኑ እምነት የሚመነጭ ነው።
ሬፍ ፓስተር በጡረታ ላይ ያለች
ማሪያን ከ1968 እስከ 1969 ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በነርስነት በመስራቷ ከሀገሪቷ ጋር በጣም ተላምዳለች፡፡ የብዙ አመት ትጋቷ፣ እውቀቷ እና በልምድ የካበተ ህይወቷ ማሪያን የተቋሙ ጠቃሚ ምሶሶ እንድትሆን አድርጓታል፡፡
ኦኮፔሽናል ቴራፒስት፣ የዊልቸር ስፔሻሊስት
ለ20 አመታት ያክል የሆክንስ ሮል አግ የዊልቸር ድርጅት ባለቤት ነበር፡፡ በተሃድሶ ቴክኖሎጂ የስልጠና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ረገድ ሚና ይጫወታል፡፡ እና እስከ 2010 ድረስ ሮሌድ የተሰኝው አጋር ድርጅት ዳይሬክተር ነበር፡፡
አስተማሪ እና የልዩ ክህሎት አስተማሪ
ክርስቲን ኦብሪል የ30 አመታት የማስተማር እና የልዩ ትምህርት ልምድ አላት፡፡ በአርት እና በእደ ጥበባት ዘርፍ ብዙ አመታትን አሳልፋለች፡፡ የብቁነት እድገት ፕሮግራም እና የተሃድሶ ዘርፉ ተጠሪ ናት፡፡
አዲስ ጉዞ ስዊዘርላንዳዊ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አካል ጉዳተኞች ጋር አብሮ ይሰራል።
Copyright ©2023. Addis Guzo
Design by Negat Creative