ቤተሰብን ያማከለ የቅድመ
ተደራሽነት ፕሮግራም

ቤተሰብን ያማከለ የቅድመ ተደራሽነት ፕሮግራም ብዙ አይነት የአካል ጉዳት ያለባቸው ህጻናት እና ልጆች ላላቸው ቤተሰቦች ይሰጣል፡፡ በሙሉ ቤተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የልጆቻቸውን እድገት በጥሩ ሁኔታ እንዲደግፉ ለእያንዳንዱ ልጅ እና እንክብካቤ ሰጪ ለሆኑ መሪዎች የተናጠል የህክምና ፕሮግራም አዘጋጅተናል፡፡

ባለብዙ ዘርፍ የሆነው የህክምና ፕሮግራም እነዚህን ያካትታል፡-

° አካላዊ ህክምና

° ተግባራዊ የተግባቦት እና ጨዋታዎችን መላመድ

° የስራ ህክምና እና የሰውነት የስሜት ህዋሳትን ብሎም እንቅስቃሴን ማነቃቃት

° ለቤት ውስጥ ጥቅም የግለሰብ የህክምና ፕሮግራምን ማዘጋጀት እና መገምገም

° በመብላት እና የመዋጥ ስልጠና፣ ከጭንቀት የሚመጣ ጨጓራን መከላከል፣ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ስልጠና፣ አያያዝ፣ ብዙ የአካል ጉዳት ያለባቸው ህጻናትን መሸከም እና መያዝ በመሳሰሉት ርእሶች ላይ የወርክሾፕ ስልጠና መስጠት፡፡ 

የፊዚዮቴራፒ
ሕክምና

የተሃድሶ ቡድናችን ትክክለኛ ጊዜ የብዙ ዘርፍ ሙያን ባካተቱ ከውጪ ሀገር በመጡ ባለሙያዎች እና የዘመነ እውቀት እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ የእድገት ስልጠና ያገኛል፡፡ የህጻናት፣ የወጣቶች እና የአዋቂዎች የፊዚዮቴራፒ ህክምና በእድሜያቸው ወይም በአካል ጉዳት አይነታቸው በቅድመ ተደራሽነት ፕሮግራማችን ላልተካተቱ ህጻናት ብሎም ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች በተናጠል የፊዚዮቴራፒ ህክምና እንሰጣለን፡፡ በደንብ በተደራጀው ማእከላችን የተለያዩ መሳሪያዎች እና ድጋፎች አሉ፡፡

አካታች የሆነ
የመጫወቻ ሜዳ

አካታች የሆነ የመጫወቻ ሜዳ/የአካል ጉዳት ላለባቸው እና ለሌለባቸው ልጆች የሴንሰሪ እና የመጫወቻ መናፈሻ በህዳር 2012 ከኩኩክ የባህል ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ከተግዳሮት ነጻ የሆነ የመጫወቻ ሜዳን ገንብተናል፡፡ በአካባቢው ከሚገኙ የተፈጥሮ እቃዎች በመጠቀም ብቻ በህክምና፣ትምህርት እና የስነ-ምህዳር ዘርፎችን ባማከለ ሁኔታ ነበር የተገነባው፡፡ ከቤት ውጪ የሆነው የመጫወቻ ስፍራ በተሃድሶ ፕሮግራም ውስጥ ላሉት ልጆች አዲስ የስሜት ህዋሳት የማነቃቃት እና የእንቅስቃሴ ልምምድ ብቃትን እንዲለማመዱ ያደርጋል፡፡ ለወደፊቱ በአካባቢው ያሉ ልጆች መጫወቻ ሜዳችን መተው እንዲጫወቱ እንጋብዛለን፡፡ ይህም የአካል ጉዳት ያለባቸው እና የሌለበናቸው ልጆች የሚኖራቸውን ቅርርብ ያጎለብታል፡፡

በሙያዎች የሚደረግ
ትብብር

በሙያዎች የሚደረግ ትብብር ቅድመ ተደራሽነት እና አካላዊ ህክምና በሙያዎች መካከል የሚደረግ ትብብር በጣም ወሳኝ ነው፡፡ የዊልቸር መካኒኮቻችን እና የተሃድሶ ቡድኑ ድጋፍ ሰጪ የሆኑ መሳሪያዎችን ለማቅረብ አንድ ላይ በቅርበት ይሰራሉ፡፡ ከዚህ ልጆች ብቻ አይደሉም ተጠቃሚ የሚሆኑት፡፡ በሚደረገው ልውውጥ ቡድኑ ሙያዊ ብቃታቸውን እና ክህሎታቸውን ያሰፋሉ እና ያጎለብታሉ፡፡