የአዲስ ጉዞ
ማህበር

አዲስ ጉዞ አሁን ላይ 46 አባላት ያሉት በስዊዝ እውቅናን ያገኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ ከ2004 ጀምሮ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ማእከል በመሆን ሰርተናል፡፡ እና በኦሮሚያ ክልል ዙሪያ ላሉ 5 ከተሞች ድጋፍ አድርገናል፡፡  ይህም አዳማ፣ ፊድጄ፣ ቢሾፍቱ፣ አምቦ እና ሰበታን ያካትታል፡፡ ጾታቸው፣ እድሜያቸው፣ ማህበራዊ ዝናባሌያቸው፣ የፖለቲካ እይታቸው ወይም ሀይማኖታዊ እምነታቸው ምንም ይሁን ምን ከአካል ጉዳት ጋር ያሉ ሰዎች አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የተቋሙ ከፍተኛ አካል ጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኘው ፕሮጀክት የስልት እና የቴክኒክ አስተዳደር ብሎም አስፈላጊ የሆኑ ገንዘቦችን የማሰባሰብ ኃላፊነት አለበት፡፡ የአሰራር አስተዳደሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የካንትሪ ዳይሬክተሩ እና የሱ አስተዳደር ቡድኖች ኃላፊነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሰራተኞቹ በኢትዮጵያ የሰራተኛ እና አሰሪ ህግ መሰረት ይቀጠራሉ፡፡

አዲስ ጉዞ በሲቪል ማህበራት ድርጅቶች አዋጅ መሰረት የተመዘገበ እና እንደ ውጪ ድርጅት  በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታወቅ ነው፡፡