በርናንድ “ቤኒ ዊስለር እና ክርስቲን ኦበርሊ” በጊዜው ጥቅም ላይ የዋሉ ዊልቸሮችን ከስዊዘርላንድ ወደ ኢትዮጵያ በሚያቀርብ የእርዳታ ፕሮጀክት ውስጥ በአዲስ አበባ ከ1999 እስከ 2002 በበጎ ፍቃደኝነት ሰርተዋል፡፡
ክሪስቲን እና ቤኔ ከማሪያን ሎቸር ጋር በመሆን በርን የሚገኘውን የአዲስ ጉዞ ማህበር አግኝተው በአዲስ አበባ የዊልቸር ወርክሾ መስርተዋል፡፡
በጦርነት የተፈናቀሉ ሰዎች በሚገኙበት ማእከል ውስጥ የመሰረት ድንጋይ የመጣል ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከፍተኛ የሆነ የዛገ ብረት ተወግዶ እና ለብዙ ሰአት ብየዳ ከተከናወነ በኋላ ላረጀ ኮንቴነተር የዊልቸር ወርክሾፑ ተገንብቷል፡፡
አዲስ ጉዞ እንደ ውጪ ድርጅት እውቅናን አግኝቷል እና ቢሮ ከፍቷል፡፡
የዊልቸር ባስኬትቦል የስፖርት ሜዳ ተገንብቷል፡፡
የመጀመሪያው የአነስተኛ የስራ እድል ፈጣሪዎች ቡድን ስልጠና ተጀምሯል፡፡
የአካል ጉዳት ላለባቸው ልጆች ወላጆች ማዋያ ተገንብቷል እና የአዋቂዎች ፊዚዮቴራፒ ቀጥሏል፡
በአዲስ የፕሮጀክት ስፍራ ላይ የስራ ፈጣራ ስራዎች ተጀምሯል፡፡ የአዲስ ጉዞ ጊዜያዊ የዳንስ ቡድን ተመሰረተ፡፡
አዲሱ የፕሮጀክት ሳይት የመመረቅ እና የመጀመር ስራ ተከናውኗል፡፡ በዚያው አመት በኢትዮጵያ ውስጥ አካታች የሆነ ሜዳን ለመገንባት ከኩኩክ የባህል ማህበር ጋር አጋር ሆነናል፡፡
ኮሮና! ተገቢ የሆነ መከላከያ በመተግበር ሳናቋርጥ ስራችንን ቀጥለናል፡፡
በተሃድሶ መምሪያችን በልጆች እና በታዳጊዎች ፊዚዮቴራፒ ስፔሻላይዝ አድርገናል እና ቤተሰብን ያማከለ የቅድመ ተደራሽነት ፕሮግራምን አስጀምረናል፡፡
በአጭር አመታት አዲስ ጉዞ ከዊልቸር ወርክሾፕ ተነስቶ ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች የልህቀት ማእከል ወደ መሆን ተሻግሯል፡፡
አዲስ ጉዞ ስዊዘርላንዳዊ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አካል ጉዳተኞች ጋር አብሮ ይሰራል።
Copyright ©2023. Addis Guzo
Design by Negat Creative