የጥቃቅን -ንግድ
ቡድን ለሴቶች

በኢትዮጵያ ውስጥ መንቀሳቀስ ለማይችሉ ሰዎች ትምህርት ለማግኘት፣ ስራ ለመፈለግ ወይም ቢዝነስ ለመምራት በጣም ከባድ ነው፡፡ ላለፉት 8 አመታት በተለያዩ ንግዶች 80 የሚጠጉ ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሰዎችን አሰልጥነናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ንግድ ጀምረዋል፡፡ ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሰዎች የሕይወት ሁኔታ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እና እድገትን ለማስመዝገብ ፈታኝ በመሆኑ ምክንያት መሀከለኛ ስኬት ነው ያስመዘገቡት፡፡ ይህንን ልምድ በመመርኮዝ ከሶስት የተለያዩ የዕደ-ጥበባት ቡድኖች (ከሃያዶል፣ከሰፊ ሲስተርስ እና ከጩጩራ) ለተውጣጡ ለአስራ አንድ ሴቶች ተደራሽ የሆኑ ወርክሾፖቻችንን ማጓጓዣ እና ከስልጠናዎቻቸው በኋላ በሁሉም የስራ ፈጠራ ዘርፎች ምክርን መስጠታችንን ቀጥለናል፡፡ አሻንጉሊት መስራት፣ ልብስ ስፌት እና የጥልፍ (ኪሮሽ) ስራ ለብዙ አመታት በእኛ ዘንድ ስልጠናን ወስደዋል፡፡ ከአዲስ ጉዞ ጥላ ስር የቦትል ብሩሽ ክራፍት ሴንተር ኮፕሬቲቭ ለመመስረት በጋራ ተሰባስበዋል፡፡ በዚህ መንገድ ብቻ ነው ንግዳቸውን በውጤታማነት መምራት እና ቋሚ የሆነ ገቢን ማረጋገጥ የሚችሉት፡፡ ዛሬ ላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶቻቸውን በእጅ የተሰሩ ዕደ-ጥበባት፣ ሱቆች ወይም ባዛሮች በፕሮጀክት ስፍራችን በቀጥታ ይሸጣሉ፡፡ ከእነዚህ ቡድኖች አንደኛዋ አሁን ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ሌሎች ቡድኖችን ታሰለጥናለች፡፡

ክህሎቶችን
ማሻሻል

የሕይወት ክህሎቶች ለመከላከል፣ ጤናን እና የግል እድገትን ለማጎልበት ወሳኝ የሆነ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ሰዎች የእለት ተእለት የሕይወት ጥያቄዎችን እና ተግዳሮቶችን በራሳቸው እና በውጤታማነት እንዲወጡ ያስችላሉ፡፡ ብዙዎቹ የአገለግሎታችን ተጠቃሚዎች በትምህርት እጦት እና ለብዙ አመታት በመገለል ምክንያት የሚጠቅሟቸውን መሰረታዊ የሆኑ ተሞክሮዎች እና መረጃዎችን አጥተዋል፡፡ የክህሎት ስልጠናዎቻችን ከተሃድሶ ፕሮግራም፣ በጠርሙስ ስራ የዕደ-ጥበብ ማእከል ላሉት ሴቶች እና ለስፖርት እና የዳንስ ቡድኑ አባላት የተውጣጡ ቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች ያማከለ ነው፡፡ ሰዎች ራሳቸውን እንዲረዱ ማገዝ በሚለው በዚህ እሳቤ ስር እንደ ጤና ጉዳዮች፣ የጾታ ጉዳዮች፣ የሴቶች ጉዳዮች፣ ጥቃትን መከላከል እና ህጻናትን መንከባከብ የመሳሰሉት ርእሰ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ፡፡

የዊልቸር የቅርጫት
ኳስ ስፖርቶች

የዊልቸር ወርክሾፑ እንደተከፈተ ወዲያው በ2005 የዊልቸር ቅርጫት ኳስ የስፖርት ሜዳ ገንብተናል፡፡ ከዚያ አንስቶ ንጹህ የሆነ ደስታ፣ ሀይል እና የቡድን መንፈስ በአዲስ ጉዞ የእለት ተእለት ህይወት ውስጥ ጎልብቷል፡፡ ይህ ስፖርት በእለት ተእለት ህይወታቸው ውስጥ ያሉት ተግባራትን በተሻለ መንገድ እንዲወጡ ተሳታፊዎቹን በአካላዊ እና በስነ-ልቦናዊ እንዲጠነክሩ ለማድረግ የታለመ ነው፡፡ ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በቅርበት በመተባበር እስካሁን ድረስ 18 የወንድ እና 14 የሴት ተሳታፊዎች ያሉት ሁለት የዊልቸር የቅርጫት ኳስ ቡድን መስርተናል፡፡ ቡድናችን በመደበኛነት ይሳተፋል እና በውድድሮች ላይ በጣም ውጤታማ ነው ብሎም ለአመታት በሀገሪቱ ውስጥ ምርጡ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ሳምንታዊ ልምምዶች የአካል ጉዳተኛ በሆኑ እና ባልሆኑ ሙያው ባላቸው የአሰልጣኞች ቡድን ይመራል፡፡

አርት-ዘመናዊ
ዳንስ

በ2010 የአዲስ ጉዞ የዳንስ ቡድን ተመሰረተ፣ ወዲያውኑ ዘመናዊ ዳንስን የዳንስ መገለጫችን አድርገን መረጥን፡፡ አካላዊ እና ስሜታዊ መግለጫዎችን ያበረታታል እና በእንቅስቃሴ እና በፈጠራ የግል ነጻነትን ለማግኘት ይረዳል፡፡ ከግል የሰውነት እንቅስቃሴ እና ስብእናቸው የሚመነጭ የተለየ የዳንስ አገላለጾችን ያሳያሉ፡፡

በዚህ አካል ጉዳተኛነታቸውን ይሸፍናል፡፡ አካላዊ ውስንነት መሬት ውስጥ ይቀበራል፡፡ ለብዙዎቹ ተሳታፊዎች ይህ ያልተጠበቀ ልምምድ ነው፡፡ ሁለት የዳንስ ቡድኖች (አስራ ሁለት) ጀማሪዎች እና ሰባት ልምድ ያላቸው ደናሾች በዳንስ ስቱዲዮዋችን ውስጥ በሳምንት ሁለቴ ይለማመዳሉ እና አካል ጉዳተኛ በሆኑ እና ባልሆኑ ልምድ ባላቸው የዳንስ አሰልጣኞች ይሰለጥናሉ፡፡ በዳንስ አቀራረብ ማህበራዊ ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች እውቅና መስጠትን እናጎለብታለን ብሎም ለረዥም ጊዜ የአካታችነት ጉዞዋችን ወሳኝ የሆነ አስተዋጽኦን ያደርጋል፡፡