ቤተሰብን ያማከለ የቅድመ
ተደራሽነት ፕሮግራም

ቤተሰብን ያማከለ የቅድመ ተደራሽነት ፕሮግራም ብዙ አይነት የአካል ጉዳት ያለባቸው ህጻናት እና ልጆች ላላቸው ቤተሰቦች ይሰጣል፡፡ በሙሉ ቤተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የልጆቻቸውን እድገት በጥሩ ሁኔታ እንዲደግፉ ለእያንዳንዱ ልጅ እና እንክብካቤ ሰጪ ለሆኑ መሪዎች የተናጠል የህክምና ፕሮግራም አዘጋጅተናል፡፡

ባለብዙ ዘርፍ የሆነው የህክምና ፕሮግራም እነዚህን ያካትታል፡-

° አካላዊ ህክምና

° ተግባራዊ የተግባቦት እና ጨዋታዎችን መላመድ

° የስራ ህክምና እና የሰውነት የስሜት ህዋሳትን ብሎም እንቅስቃሴን ማነቃቃት

° ለቤት ውስጥ ጥቅም የግለሰብ የህክምና ፕሮግራምን ማዘጋጀት እና መገምገም

° በመብላት እና የመዋጥ ስልጠና፣ ከጭንቀት የሚመጣ ጨጓራን መከላከል፣ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ስልጠና፣ አያያዝ፣ ብዙ የአካል ጉዳት ያለባቸው ህጻናትን መሸከም እና መያዝ በመሳሰሉት ርእሶች ላይ የወርክሾፕ ስልጠና መስጠት፡፡