የዊልቸር የቅርጫት
ኳስ ስፖርቶች

የዊልቸር ወርክሾፑ እንደተከፈተ ወዲያው በ2005 የዊልቸር ቅርጫት ኳስ የስፖርት ሜዳ ገንብተናል፡፡ ከዚያ አንስቶ ንጹህ የሆነ ደስታ፣ ሀይል እና የቡድን መንፈስ በአዲስ ጉዞ የእለት ተእለት ህይወት ውስጥ ጎልብቷል፡፡ ይህ ስፖርት በእለት ተእለት ህይወታቸው ውስጥ ያሉት ተግባራትን በተሻለ መንገድ እንዲወጡ ተሳታፊዎቹን በአካላዊ እና በስነ-ልቦናዊ እንዲጠነክሩ ለማድረግ የታለመ ነው፡፡ ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በቅርበት በመተባበር እስካሁን ድረስ 18 የወንድ እና 14 የሴት ተሳታፊዎች ያሉት ሁለት የዊልቸር የቅርጫት ኳስ ቡድን መስርተናል፡፡ ቡድናችን በመደበኛነት ይሳተፋል እና በውድድሮች ላይ በጣም ውጤታማ ነው ብሎም ለአመታት በሀገሪቱ ውስጥ ምርጡ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ሳምንታዊ ልምምዶች የአካል ጉዳተኛ በሆኑ እና ባልሆኑ ሙያው ባላቸው የአሰልጣኞች ቡድን ይመራል፡፡